ኢዮብ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተዋረዱትን በክብር ከፍ ያደርጋቸዋል፤ ያዘኑትንም በማጽናናት ደስ ያሰኛቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተዋረዱትን በከፍታ ቦታ ያስቀምጣል፤ ያዘኑትንም ወደ አስተማማኝ ስፍራ ያወጣቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተዋረዱትን ወደ ላይ ያወጣል፥ ያዘኑትን ለደኅንነት ከፍ ያደርጋቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋቸዋል፥ የወደቁትንም ያነሣቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተዋረዱትን ወደ ላይ ያወጣል፥ ኀዘንተኞችንም ለደኅንነት ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል። |
በምድሪቱ ያሉ ዛፎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ ረጃጅም ዛፎችን አሳጥራለሁ፤ አጫጭር ዛፎችንም ከፍ ብለው እንዲያድጉ አደርጋለሁ፤ እኔ ለምለም ዛፎችን አደርቃለሁ፤ ደረቅ ዛፎችንም አለመልማለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ አደርጋለሁ ያልኩትንም ሁሉ እፈጽማለሁ።”
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤
ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብር የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ እርሱ ራሱ ከተቀበላችሁት መከራ ያድናችኋል፤ ይደግፋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።