ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።
ኢዮብ 42:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላክ ሆይ! አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል ዐውቃለሁ፤ የአንተንም ዕቅድ ማሰናከል የሚችል የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣ ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሁሉንም ማድረግ እንድምትችል፥ ሐሳብህም ሊከለከል ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ የሚሳንህም እንደሌለ ዐወቅሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። |
ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።
እግዚአብሔር የሠራው ነገር ሁሉ ዘለዓለማዊነት እንዳለው ዐውቃለሁ፤ በእርሱ ላይ የሚጨመርበት ወይም ከእርሱ የሚቀነስ ነገር የለም፤ እግዚአብሔር ይህን ያደረገው ሰዎች እርሱን እንዲፈሩት ነው።
የሠራዊት አምላክ ይህን ሁሉ ለማድረግ ወስኖአል፤ ይህ እንዳይሆን የሚያደርግ ማነው? ለመቅጣትም ክንዱን ዘርግቶአል፤ ተከላክሎ ሊያቆመው የሚችልስ ማን ነው?
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።
ከሕዝብ መካከል ተባረህ መኖሪያህ ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ ይህም የሚሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ነው።”
በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።
ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመልክቶ፦ “እርግጥ ይህ ነገር በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል፤ ለእግዚአብሔር ሁሉ ነገር ይቻለዋል፤” አላቸው።
እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፥ ሁሉ ነገር ይቻልሃል፤ ይህን የመከራ ጽዋ ከእኔ አርቅልኝ፤ ነገር ግን እንደ አንተ ፈቃድ እንጂ እንደ እኔ ፈቃድ አይሁን።”
ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤