La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 4:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጠዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፤ ሳይታወቅ ለዘለዓለም ይጠፋሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በንጋትና በምሽት መካከል ይደቅቃሉ፤ ሳይታሰብም ለዘላለም ይጠፋሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በጥዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፥ ማንም ሳያስብ ለዘለዓለም ይጠፋሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከጥ​ዋት እስከ ማታ አይ​ኖ​ሩም። ራሳ​ቸ​ውን ማዳ​ንና መር​ዳት አይ​ች​ሉ​ምና ጠፉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በጥዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፥ ማንም ሳያስብ ለዘላለም ይጠፋሉ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 4:20
14 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ችግርን ሁሉ ያመጣባቸው ስለ ነበር አንዱ ሕዝብ ሌላውን ሕዝብ አንዲቱ ከተማ ሌላይቱን ከተማ ያጠፉ ነበር።


ኢዮራም በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ስምንት ዓመት ገዛ፤ እርሱ በሞተ ጊዜ ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።


ሰው ከሞተ በኋላ በሕይወተ ሥጋ ሊኖር ይችላልን? ዕረፍቴ እስከምትመጣበት ጊዜ ድረስ፥ ይህን የትግል ዘመኔን ፍጻሜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።


እንደ አበባ ታይቶ ወዲያውኑ ይረግፋል፤ እንደ ጥላም ብዙ ሳይቈይ ወዲያው ያልፋል።


ኀይልህ ለዘለዓለም በእርሱ ላይ ይበረታል፤ እርሱም እንዳልነበረ ይሆናል፤ መልኩንም ለውጠህ ከፊትህ ታስወግደዋለህ።


የዕድሜዬ ፍጻሜ እየተቃረበ ነው፤ ወደማልመለስበት መንገድ ለመሄድ ጥቂት ዘመን ብቻ ይቀረኛል።


በምድር ላይ የሚያስታውሰው አይኖርም። ዝናውም ከምድር ይጠፋል።


እርሱ እንደ ራሱ ኩስ በፍጹም ይጠረጋል፤ ያዩት የነበሩ ሰዎችም ወዴት ነው? ይላሉ።


ነገር ግን ቈይቼ ብመለስ ከስፍራው አጣሁት፤ ብፈልገውም ላገኘው አልቻልኩም።


ወደማልመለስበት ወደ ሞት ሳልሄድ ጥቂት ደስታ እንዳገኝ እባክህ ታገሠኝ።


ክፉዎች እንደ ሣር ቶሎ ቢያድጉም፥ ክፉ አድራጊዎች ቢበለጽጉም፥ እነርሱ ለዘለዓለሙ ይጠፋሉ።


የጻድቅ ሰው መታሰቢያ ለበረከት ይሆናል የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።