ተንበርክካ በማማጥ ግልገሎችዋን የምትወልደው መቼ እንደ ሆነ ታውቃለህን?
ተንበርክከው ይወልዳሉ፤ ከምጣቸውም ጣር ይገላገላሉ።
ይንበረከካሉ፥ ልጆቻቸውንም ይወልዳሉ፥ ከምጣቸውም ያርፋሉ።
ልጆቻቸውንስ ያለ ፍርሃት አሳድገሃልን? መከራቸውንስ አስወግደሃልን?
በእርግዝና ምን ያኽል ጊዜ እንደምትቈይ፥ መቼስ እንደምትወልድ ታውቃለህን?
ግልገሎችዋ በዱር አድገው ይጠነክራሉ፤ ወጥተውም ከሄዱ በኋላ፥ ዳግመኛ ወደ እናታቸው አይመለሱም።