ኢዮብ 39:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርግዝና ምን ያኽል ጊዜ እንደምትቈይ፥ መቼስ እንደምትወልድ ታውቃለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደ ሆነ ትቈጥራለህን? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሷ የሚወስዱባትንስ ወራት መቁጠር ትችላለህን? የምትወልድበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋ የምትወልድበትንስ ሙሉ ወራት ትቈጥራለህን? ከምጥስ ትገላግላታለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋ የምትፈጽመውንስ ወራት ትቈጥራለህን? የምትወልድበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? |
በበረሓ መኖርን የለመደች የሜዳ አህያ፥ ፍትወት በተቀሰቀሰባት ጊዜ ማን ሊቈጣጠራት ይችላል? ወንዶች የሜዳ አህዮች ያሉበትን ስፍራ፥ ራስዋ አነፍንፋ ስለምትደርስበት፥ እነርሱ እርስዋን በመፈለግ መድከም አያስፈልጋቸውም።