ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የአባቱ የሰሎሞን አማካሪዎች የነበሩትን ሽማግሌዎች በአንድነት ሰብስቦ “እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ መልስ መስጠት እንድችል ምን ትመክሩኛላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
ኢዮብ 32:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ሽማግሌዎች በቅድሚያ ይናገሩ፤ በረጅም ዕድሜ ያገኙትን ጥበብ ያስተምሩ’ ብዬ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ዕድሜ ይናገራል፤ ረዥም ዘመን ጥበብን ያስተምራል’ ብዬ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደዚህም አልሁ፦ ‘ዕድሜ ይናገር፥ ረጅም ዕድሜም ጥበብን ያስታውቅ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህም አልሁ፥ “የሚናገሩ ዓመታት አይደሉም፥ በዓመታት ብዛት ሰዎች ጥበብን አያውቋትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህም አልሁ፦ ዓመታት በተናገሩ ነበር፥ የዓመታትም ብዛት ጥበብን ባስተማረች ነበር። |
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የአባቱ የሰሎሞን አማካሪዎች የነበሩትን ሽማግሌዎች በአንድነት ሰብስቦ “እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ መልስ መስጠት እንድችል ምን ትመክሩኛላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
እስከ አሁን በነበረው ጊዜ እናንተ አስተማሪዎች መሆን በተገባችሁ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የመጀመሪያውን ትምህርት ሌላ ሰው እንደገና እንዲያስተምራችሁ ያስፈልጋል፤ በዚህ ዐይነት የሚያስፈልጋችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።