ኢዮብ 32:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስቱ ሰዎች ለኢዮብ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት አለመቻላቸውን በማየቱ እጅግ ተቈጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ኤሊሁ እነዚህ ሦስቱ የሚሉትን ባጡ ጊዜ ቍጣው ነደደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሊሁም በነዚህ በሦስቱ ሰዎች አንደበት መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ ቁጣው ነደደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤሊዩስም በእነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ በቍጣው ተቈጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤሊሁም በነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ ቍጣው ነደደ። |
ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር።