ኢዮብ 32:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የራም ቤተሰብ የነበረው ቡዛዊው የባራኬል ልጅ ኤሊሁ ኢዮብ ራሱን ከእግዚአብሔር አብልጦ ጻድቅ ስላደረገ ተቈጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከራም ወገን የሆነው፣ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ግን ኢዮብ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ ስላደረገ እጅግ ተቈጣው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቁጣ ነደደ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቍጣ ነደደ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው። |
ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።