ኢዮብ 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስረኞች እንኳ ሰላም ያገኛሉ፤ የአሠሪዎቻቸውን የቊጣ ድምፅ ከመስማት ይድናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምርኮኞች እንደ ልባቸው ይቀመጣሉ፤ ከእንግዲህም የአስጨናቂዎቻቸውን ጩኸት አይሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ግዞተኞች በአንድነት ተዘልለው ተቀምጠዋል፥ የአስጨናቂውን ድምፅ አይሰሙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም የጥንት ዘመን ሰዎች በአንድነት፥ የአስጨናቂውን ድምፅ አይሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ግዞተኞች በአንድነት ተዘልለው ተቀምጠዋል፥ የአስጨናቂውን ድምፅ አይሰሙም። |
ያቢን ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎች ነበሩት፤ የእስራኤል ሕዝብ በጭካኔና በዐመፅ ለኻያ ዓመት ገዛቸው፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።