ኢዮብ 27:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከሥጋቸው በመለየት ዕድሜአቸውን ባሳጠረ ጊዜ፥ እግዚአብሔርን የሚክዱ ሰዎች ምን ተስፋ ይኖራቸዋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሲያስወግደው፣ ነፍሱንም ሲወስድበት ዐመፀኛ ምን ተስፋ አለው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በወሰደ ጊዜ፥ አምላክን የካደ ሰው ተስፋው ምንድነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኀጢአተኛ ድኅነትን ተስፋ ያደርግ ዘንድ ለምን ደጅ ይጠናል? በእግዚአብሔርስ የማያምን ይድናልን? እንጃ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥ የዝንጉ ሰው ተስፋው ምንድር ነው? |
“ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገባ፥ በሩን የምትዘጉ እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ!” [
እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን እንደማይሰማ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱንም የሚፈጽም ሰው ሲኖር እርሱን እግዚአብሔር ይሰማዋል።
ያ ዘመን በደረሰ ጊዜ የመረጣችሁት ንጉሥ ስለሚፈጽምባችሁ በደል በመረረ ሁኔታ ማጒረምረም ትጀምራላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን አቤቱታችሁን አያዳምጥም።”