ኢዮብ 22:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞችህን ያለ አንዳች ምክንያት በዋስትና አስይዘሃቸዋል፤ ሌሎችንም ልብሳቸውን ገፈህ ራቊታቸውን አስቀርተሃቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ ሰዎችን ገፍፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወንድሞችህ አላግባብ መያዣ ወስደሃል፥ የታረዙትንም ልብስ ዘርፈሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድሞችህን መያዣ በከንቱ ወስደሃል፥ የታረዘውንም ልብሱን ገፍፈሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድሞችህን መያዣ በከንቱ ወስደሃል፥ የእርዘኞቹንም ልብስ ዘርፈሃል። |
ድኾችንና ችግረኞችን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማ፥ ገንዘብ ሲያበድር በመያዣ ስም የወሰደውን ቢያስቀር፥ በአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች ጣዖትን ቢያመልክ አጸያፊ ነገሮችን ቢያደርግ፥
ዕዳቸውን መክፈል ከማይችሉ ድኾች ላይ ልብሳቸውን መያዣ አድርገው ይወስዳሉ፤ መሥዋዕት በሚያቀርቡበትም ቦታ ሁሉ ይተኙበታል፤ ከባለ ዕዳዎች በመቀጫ ስም የወሰዱትን የወይን ጠጅ በአምላካቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ይጠጣሉ።
“ለአንድ ሰው ብድር በምታበድርበት ጊዜ የእህል ወፍጮውን ወይም መጁን መያዣ አድርገህ አትውሰድበት፤ ይህን ማድረግ ሕይወትን እንደ መያዣ አድርጎ እንደ መውሰድ ይቈጠራል።