ኢዮብ 22:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሁሉ የደረሰብህ ክፋትህ ስለ በዛና ኃጢአትህም ወሰን የሌለው ስለ ሆነ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፋትህ ታላቅ፣ ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፋትህስ ብዙ አይደለምን? ለዐመፅህም ወሰን የለውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ክፋትህስ የበዛ አይደለምን? ኀጢአትህስ ቍጥር የሌለው አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፋትህስ የበዛ አይደለምን? ለኃጢአትህም ፍጻሜ የላትም። |
ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል! በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤ እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።