አንድ ጊዜ ለመናገር ዕድል ስጡኝ፤ ከዚያ በኋላ እንደ ፈለጋችሁ መሳለቅ ትችላላችሁ።
አኔ ስናገር ታገሡኝ፤ ከተናገርሁ በኋላ፣ መሣለቅ ትችላላችሁ።
እናገር ዘንድ ተውኝ፥ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።
እናገር ዘንድ ዝም በሉ፤ ከተናገርሁ በኋላ ትስቁብኛላችሁና፤
ኢዮብ ሆይ! ከንቱ ንግግርህ መልስ የማይሰጥበት ይመስልሃልን? ይህን ያኽልስ ስታፌዝ፥ የሚገሥጽህ የሌለ መሰለህን?
እስቲ ዝም በሉ እኔም እንድናገር ዕድል ስጡኝ ከዚያ በኋላ የፈለገው ነገር ይሁን።
እግዚአብሔር ቢመረምራችሁ አንዳች መልካም ነገር ያገኝባችኋልን? ሰዎችን እንደምታሞኙ እግዚአብሔርንም ማሞኘት የምትችሉ ይመስላችኋልን?
ሰዎች በዙሪያዬ ተሰብስበው ተዘባበቱብኝ፤ እያፌዙም በጥፊ መቱኝ።
ወዳጆቼ በንቀት ይመለከቱኛል፤ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር አለቅሳለሁ።
የሚሳለቁብኝ ከበቡኝ ዐይኔም የእነርሱን ጥላቻ ይመለከታል።
“እስቲ ንግግሬን በጥሞና አድምጡኝ፤ በዚህም እኔን እንዳጽናናችሁኝ ይቈጠርላችሁ።
እናንተም እኮ ይህን ሁሉ ታውቃላችሁ፤ ታዲያ ይህን ከንቱ ነገር ለምን ትናገራላችሁ?”