ኢዮብ 18:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! ለምን እንደዚህ ንግግር ታበዛለህ? እስቲ አድምጥ፤ እኛም እንናገር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ንግግር የምትጨርሰው መቼ ነው? እስኪ ልብ ግዛ፤ ከዚያ በኋላ እንነጋገራለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እስከ መቼ ቃላትን ታበዛለህ? አስተውል፥ ከዚያም እኛ እንናገራለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው? እኛም እንድንነግርህ ታገሥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ መቼ ቃልን ታጠምዳለህ? አስተውል፥ ከዚያም በኋላ እንናገራለን። |