La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 17:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሐዘን የተነሣ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤ መላ ሰውነቴም እንደ ጥላ ሆኖአል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤ መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ መላ ሰውነቴ እንደ ጥላ ሆነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዐይ​ኖች ከእ​ንባ የተ​ነሣ ፈዘዙ፥ ሁሉም እጅግ ተጸ​የ​ፉኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ ብልቶቼም ሁሉ እንደ ጥላ ሆኑ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 17:7
10 Referencias Cruzadas  

ፊቴ በልቅሶ ቀላ ድቅድቅ ጨለማም ቅንድቦቼን ሸፈናቸው።


ወዳጆቼ በንቀት ይመለከቱኛል፤ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር አለቅሳለሁ።


የሰውነቴ መጨማደድ ማስረጃ ሆኖብኛል፤ ክሳቴም በእኔ ላይ ተነሥቶ ኃጢአተኛ ነህ ብሎ ይመሰክርብኛል።


መላ ሰውነቴ በትል ተሞልቶአል፤ ሥጋዬም በቅርፊት ተሸፍኖአል፤ ፈንድቶም ይመግላል።


እንደ ማታ ጥላ ላልፍ ተቃርቤአለሁ፤ እንደ አንበጣም በነፋስ ተወስጄአለሁ።


ከጠላቶቼ ተቃውሞ የተነሣ በጣም በማልቀሴ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤ ማየትም ተስኖኛል።


እግዚአብሔር የለቅሶዬን ጩኸት ሰምቶአል፤ ስለዚህ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ!


ከንቱ ሆኖ እንደ ጥላ በሚያልፍ ዘመኑ ለሰው የሚበጀውን ነገር የሚያውቅ ማን ነው? ወይስ ከሞተ በኋላ በዚህ ዓለም ምን እንደሚሆን ለሰው ማን ሊነግረው ይችላል?


በዚህ ምክንያት ልባችን ታመመ፤ በእነዚህም ነገሮች ምክንያት ዐይኖቻችን ደከሙ።