ኢዮብ 17:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገንዘብ ለማግኘት ብሎ ባልንጀራውን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ ግፉ በልጆቹ ላይ ይደርሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጥቅም ሲል ወዳጁን የሚያወግዝ፣ የልጆቹ ዐይን ይታወራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ የልጆቹ ዐይን ይጨልማል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ የልጆቹ ዐይኖች ይጨልማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ የልጆቹ ዓይን ይጨልማል። |
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
በሕዝብህ መካከል እየዞርክ የስም አጥፊነት ወሬ አታሰራጭ፤ ሰውን ወደ ሞት አደጋ የሚያደርስ ምንም ነገር አታድርግ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ።
በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍትና ለእግርህ ማሳረፊያ ቦታ አይኖርህም፤ እግዚአብሔርም የባባ ልብ፥ በናፍቆት የፈዘዘ ዐይን፥ ተስፋ የቈረጠ ስሜት ይሰጥሃል።
አንድም ጊዜ በቃላት በማቈላመጥ ወይም የገንዘብ ፍላጎት ኖሮን ከቶ እንዳልተናገርን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ምስክራችን ነው።