ኢዮብ 15:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ከምናውቀው የተለየ የምታውቀው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ተሰውሮ ለአንተ የተገለጠልህ ምን ጥበብ አለ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ? እኛስ የሌለን አንተ ያለህ ማስተዋል የቱ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ሳናውቀው አንተ የምታወቀው ምንድነው? ከእኛ ዘንድስ ሳይኖር የምታስተውለው ምንድነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ የማናውቀውን አንተ ምን ታውቃለህ? እኛስ የማናስተውለውን አንተ ምን ታስተውላለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ የማናውቀውን አንተ የምታወቀው ምንድር ነው? ከእኛ ዘንድስ የሌለው የምታስተውለው ምንድር ነው? |
እናንተ የምትመለከቱት በውጪ የሚታየውን ነገር ብቻ ነው፤ ማንም ሰው የክርስቶስ ነኝ ብሎ ቢተማመን እንደገና ያስብበት፤ እኛም እንደ እርሱ የክርስቶስ መሆናችንን ይገንዘብ።