እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን እኛም በአንተ ፊት እንግዶችና መጻተኞች ነን፤ በምድር ላይ ያለው ዘመናችን ተስፋ የሌለው እንደ ጥላ ነው።
ኢዮብ 14:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ አበባ ታይቶ ወዲያውኑ ይረግፋል፤ እንደ ጥላም ብዙ ሳይቈይ ወዲያው ያልፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ አበባ ይፈካል፥ ይረግፋልም፥ እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ አበባ ይወጣል፥ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላም ያልፋል፥ እርሱም አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ አበባ ይወጣል፥ ይረግፋልም፥ እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም። |
እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን እኛም በአንተ ፊት እንግዶችና መጻተኞች ነን፤ በምድር ላይ ያለው ዘመናችን ተስፋ የሌለው እንደ ጥላ ነው።
የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤ ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤ በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።