ኢዮብ 13:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርሱ ታደሉለታላችሁን? ለእርሱስ ጥብቅና ትቆማላችሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለርሱ ታደላላችሁን? ለእግዚአብሔር ጥብቅና ልትቆሙ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሱ እያዳላችሁ ነውን? ስለ እግዚአብሔርስ ትከራከራላችሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱ ወደ ኋላ ትመለሳላችሁን? እስኪ ራሳችሁ ፍረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለፊቱስ ታደላላችሁን? ስለ እግዚአብሔርስ ትከራከራላችሁን? |
“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።