ኢዮብ 13:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛ ሰው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ስለማይችል ምናልባት ይህ ድፍረቴ የመዳን ምክንያት ሊሆን ይችላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአተኛ በርሱ ፊት መቅረብ ስለማይችል፣ ይህ ድፍረቴ ለመዳኔ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰው በፊቱ አይቀርብምና፥ እርሱ መድኃኒት ይሆንልኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና እርሱ መድኀኒት ይሆንልኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና እርሱ መድኃኒት ይሆንልኛል። |
እግዚአብሔር በመዝሙር የማመሰግነው መከላከያ ኀይሌ ነው፤ ከጠላት እጅ ያዳነኝ ታዳጊዬም እርሱ ነው፤ እርሱ አምላኬ ስለ ሆነ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴም አምላክ ስለ ሆነ፥ ስለ ገናናነቱ እዘምራለሁ።
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።
በኮረብቶች ራስ ላይ ቅጥ ያጣ የባዕድ አምልኮ ፈንጠዝያ መፈጸማችን ምንም አልጠቀመንም፤ ለእስራኤል መዳን የሚገኘው ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው።