“ነገር ግን በእውነት እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሰዎች ጋር ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤትማ ምንኛ ያንስ?
ኢዮብ 11:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱ ታላቅነት ከሰማይ በላይ ነው፤ አንተ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ጥልቀቱም ከሲኦልም በታች ነው፤ አንተ ምን ታውቃለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፥ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፥ ምን ልታውቅ ትችላለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማይ ከፍ ያለ ነው፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ የጠለቁ ነገሮች አሉ፤ ምን ታውቃለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፥ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፥ ምን ልታውቅ ትችላለህ? |
“ነገር ግን በእውነት እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሰዎች ጋር ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤትማ ምንኛ ያንስ?
እግዚአብሔር ሆይ፥ ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤ ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።
ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤
ምድርን ቆፍረው ወደ ሙታን ዓለም ቢወርዱ እንኳ እኔ ከዚያ መንጥቄ አወጣቸዋለሁ፤ ወደ ሰማይም መጥቀው ቢወጡ እንኳ እኔ መልሼ አወርዳቸዋለሁ፤