ኤርምያስ 44:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ቦታ በምቀጣችሁ ጊዜ ‘በእናንተ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ’ ብዬ የተናገርኩት ቃል እውነት እንደሚሆን እኔ እግዚአብሔር አረጋግጥላችኋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በእናንተ ላይ አመጣለሁ ያልሁትን ክፉ ነገር እንደሚፈጸም ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሁናችሁ’ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሎቼም በእናንተ ላይ ለክፋት በእርግጥ እንደሚጸኑ እንድታውቁ በዚህች ስፍራ እቀጣችኋለሁ፤ ይህም ለእናንተ ምልክት ይሆናል፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እንደምጐበኛችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚህች ስፍራ እንድቀጣችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እኔ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ቀድሞ ጠላቱ ለነበረና ይገድለው ዘንድ ለሚፈልገው ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እንደ ሰጠሁት ሁሉ፥ ሖፍራ ተብሎ የሚጠራውን የግብጽ ንጉሥ ሊገድሉት ለሚፈልጉ ጠላቶቹ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”
ነገር ግን አገልጋዮቼ በሆኑት በነቢያት አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁ ያስተላለፍኩትን ሕግና ትእዛዝ ባለመጠበቃቸው ተቀጥተው የለምን? ስለዚህ በበደላቸው ተጸጸተው ‘የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ባቀደው መሠረት እንደ ሥራችንና እንደ አካሄዳችን በእኛ ላይ ቅጣትን ማምጣቱ ትክክለኛ ነው’ አሉ።”