ከይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ መንደሮች ሕዝቡ በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ ከብንያም ክፍል፥ ከኰረብቶች ግርጌ፥ ከተራሮችና ከይሁዳ ደቡብ ይመጣሉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላውንም መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና ዕጣን፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ጭምር ወደ ቤተ መቅደሴ ያመጣሉ።
ኤርምያስ 33:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራማው አገር በኮረብቶች ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ባሉ ከተሞች፥ በብንያም ክፍለ ግዛት፥ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉት መንደሮችና በይሁዳ የገጠር ከተሞች ሁሉ እረኞች እንደገና በጎቻቸውን ይቈጥራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተራራማው አገር፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች በብንያም አገር፣ በይሁዳ ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች መንጎች እንደ ገና በሚቈጥራቸው ሰው እጅ ሥር ያልፋሉ’ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ መንጋውን በሚቆጥረው ሰው እጅ ሥር እንደገና ያልፋሉ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቆላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም ሀገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ በተቈጣጣሪያቸው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ከይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ መንደሮች ሕዝቡ በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ ከብንያም ክፍል፥ ከኰረብቶች ግርጌ፥ ከተራሮችና ከይሁዳ ደቡብ ይመጣሉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላውንም መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና ዕጣን፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ጭምር ወደ ቤተ መቅደሴ ያመጣሉ።
ስለዚህም ተመልሰው መጥተው በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምሰጣቸውም የእህል፥ የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ የበግና የቀንድ ከብት በረከት ሁሉ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ፤ በቂ ውሃ እንዳገኘች የተክል ቦታ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ ወዲያም አያዝኑም።
ሕዝቡ መሬት ይገዛሉ፤ ውሎች ተፈርመው በምስክሮች ፊት ይታተማሉ፤ ይህም ሁሉ በብንያም ክፍል በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች፥ በይሁዳ ገጠር ከተሞች፥ በተራራማው አገር ከተሞች፥ በኮረብቶች ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ሁሉ ይፈጸማል። ሕዝቡ ሁሉ ወደ ምድራቸው ተመልሰው ንብረታቸውን እንዲረከቡ አደርጋለሁ።”
በስደት ላይ የነበሩት የሰሜን እስራኤል ሕዝብ ሖላ ከሚባል አገር ተመልሰው የከነዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ፤ በሰፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ስደተኞች በስተ ደቡብ ያሉትን ከተሞች ይይዛሉ።
“ከእናንተ መካከል መቶ በግ ያለው ሰው ከመቶዎቹ አንድ በግ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋውን እስኪያገኝ ድረስ ለመፈለግ የማይሄድ ማነው?