“በእግዚአብሔር ስም የሐሰት ትንቢት ቃል ስለሚነግሩአችሁም ስለ ቆላያ ልጅ አክዓብና ስለ ማዕሤያ ልጅ ሴዴቅያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ ‘እነርሱን ዐይናችሁ እያየ በፊታችሁ በሞት ለሚቀጣቸው ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤
ኤርምያስ 29:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያትን አስነሥቶልናል” ብላችሁ ተናግራችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም፣ “እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያት አስነሥቶልናል” ትላላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እናንተም፦ ‘ጌታ በባቢሎን ነቢያትን አስነሥቶልናል’ ብላችኋልና፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተም፦ እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያትን አስነሥቶልናል ብላችኋልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም፦ እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያትን አስነሥቶልናል ብላችኋልና፥ |
“በእግዚአብሔር ስም የሐሰት ትንቢት ቃል ስለሚነግሩአችሁም ስለ ቆላያ ልጅ አክዓብና ስለ ማዕሤያ ልጅ ሴዴቅያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ ‘እነርሱን ዐይናችሁ እያየ በፊታችሁ በሞት ለሚቀጣቸው ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤
የኔሔላም ተወላጅ ለሆነው ለሸማዕያ፥ እንዲህ በለው፤ ይህ የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ቃል ነው፤ ለኢየሩሳሌም ሰዎች ለካህኑ ለማዕሲያ ልጅ ለሰፎንያስና ለሌሎቹም ካህናት በራስህ ስም መልእክቶችን ልከሃል፤ በመልእክትህም ለሰፎንያስ እንዲህ ብለኸዋል፦
በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የእግዚአብሔር ቃል የቡዚ ልጅ ወደ ሆንኩት ወደ ካህኑ ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ ነበረ።