አህያውን በወይን ግንድ ላይ፥ ውርንጫውን በወይን ሐረግ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፥ መጐናጸፊያውን እንደ ደም በቀላ የወይን ጭማቂ ያጥባል።
ኢሳይያስ 63:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የወይን ጠጅ ጨምቆ ለማውጣት የወይን ፍሬ ሲጨምቅ እንደ ነበረ ሰው ልብስህ ስለምን ቀይ ሆነ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጐናጸፊያህ፣ ለምን በወይን መጭመቂያ፣ ወይን እንደሚረግጡ ሰዎች ልብስ ቀላ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ቀሚስህ ስለምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለምን መሰለ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጭመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ? |
አህያውን በወይን ግንድ ላይ፥ ውርንጫውን በወይን ሐረግ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፥ መጐናጸፊያውን እንደ ደም በቀላ የወይን ጭማቂ ያጥባል።
ከኤዶም ቦጽራ ቀይ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ የሚመጣው ይህ ማነው? በታላቅ ኀይሉ አስደናቂ ልብስ ለብሶ የሚራመደው ይህ ማነው? “ፍርድን የምሰጥ የማዳን ኀይል ያለኝ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ለግድያ አዘጋጃችኋለሁ፤ ገዳይም ያሳድዳችኋል፤ ደም ማፍሰስን ስላልጠላችሁ ገዳይ ያሳድዳችኋል።
ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ በብረት በትርም ይገዛቸዋል፤ እርሱ ሁሉን የሚችለውን የእግዚአብሔር አስፈሪ ቊጣ መግለጫ የሆነውን የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል፤