ኢሳይያስ 60:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ብርሃንሽ ስለሚሆን፥ ፀሐይሽ ከቶ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም ብርሃንዋን አትከለክልም፤ የመከራሽም ዘመን ያበቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይሽ ከእንግዲህ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም ብርሃን መስጠቷን አታቋርጥም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናል፤ የሐዘንሽም ቀን ያከትማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የዘለዓለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም፥ ጨረቃሽም አትገባም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የዘለዓለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ያልፋልና፤ ፀሐይሽ ከዚህ በኋላ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም አይቋረጥም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም። |
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
የሠራዊት እምላክ ስለሚነግሥ ጨረቃ ትጨልማለች፥ ፀሐይም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ እርሱ በኢየሩሳሌም፥ በጽዮን ተራራ ላይ ሆኖ ያስተዳድራል፤ የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።
ልዑል እግዚአብሔር የሞትን ኀይል ለዘለዓለም ያጠፋል! ከሰዎችም ሁሉ ዐይን እንባን ያብሳል፤ ወገኖቹ በዓለም ሁሉ ላይ የተቀበሉትን ኀፍረት ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህን ተናግሮአል።
እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም፤ እግዚአብሔር ርኅሩኅ ስለ ሆነ የእርሱን ርዳታ በመፈለግ በምትጮኹበት ጊዜ ሰምቶ መልስ ይሰጣችኋል።
በዚያን ጊዜ ጨረቃ እንደ ፀሐይ ትደምቃለች፤ የፀሐይም ብርሃን ከቀድሞ ሰባት እጅ የበለጠ ይሆናል፤ የሰባት ቀን ብርሃን ያኽልም ድምቀት ይኖረዋል፤ ይህም ሁሉ የሚሆነው እግዚአብሔር ራሱ በሕዝቡ ላይ ያመጣባቸውን ቊስል ጠግኖ በሚፈውስበት ቀን ነው።
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
ስለዚህ አንተ እግዚአብሔር የተቤዠኻቸው እየዘመሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳሉ፤ ዘላቂ ደስታንም እንደ ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ሐሴትና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ግን ከእነርሱ ይወገዳል።
በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።
ስለዚህም ተመልሰው መጥተው በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምሰጣቸውም የእህል፥ የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ የበግና የቀንድ ከብት በረከት ሁሉ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ፤ በቂ ውሃ እንዳገኘች የተክል ቦታ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ ወዲያም አያዝኑም።