ኢሳይያስ 50:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራና ለአገልጋዩ ቃል የሚታዘዝ ማነው? ብርሃን የሌለው በጨለማ የሚመላለስ በእግዚአብሔር ይታመን፤ እምነቱንም በአምላኩ ላይ ይጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው? |
እምነታቸውንም በእግዚአብሔር አድርገው እርሱ እንዲረዳቸው ተማጠኑት፤ እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ፥ በሀጋራውያንና በእነርሱም የጦር ጓደኞች ላይ ድልን አጐናጸፋቸው፤
አምላካችን ሆይ! በእኛ ላይ አደጋ ሊጥሉ በብዛት የመጡትን እነዚህን ሠራዊት ሁሉ መቋቋም ስለማንችል አንተ ራስህ ፍረድባቸው፤ የአንተን ርዳታ ለማግኘት ዐይናችንን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር ሌላ ምንም ማድረግ እንደሚገባን አናውቅም።”
ሰዎቹ በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሥተው ተቆዓ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓማ አገር ሄዱ፤ ወደዚያ ለመሄድ ጒዞ በመጀመር ላይ ሳሉም ኢዮሣፍጥ እነርሱን “የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱም ብርታትን ይሰጣችኋል፤ የእግዚአብሔር ነቢያት የሚነግሩአችሁንም እመኑ፤ ይሳካላችኋልም” አላቸው።
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሁሉ አስተዋዮች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።
በዚያን ጊዜ ከጥፋት የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ፥ ጥቃት ባደረሱባቸው በአሦራውያን ላይ አይተማመኑም፤ በዚህ ፈንታ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይተማመናሉ።
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።
ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።
ደካሞችን በቃል ማጽናትን ዐውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የምሁርን አንደበት ሰጥቶኛል፤ በየማለዳው ከእንቅልፍ ያነቃኛል፤ እንደ ተማሪም አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ይከፍታል።
ሕዝቡ እንዲህ ይላሉ፦ “ፍትሕ ከእኛ ርቆአል፤ ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም፤ ብርሃን እንዲበራልን እንፈልጋለን፤ ነገር ግን ሁሉም ጨለማ ነው፤ ስለዚህ በድቅድቅ ጨለማ እንመላለሳለን።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “የሲድራቅ፥ የሚሳቅና የአብደናጎ አምላክ የተመሰገነ ይሁን! እርሱ መልአኩን ልኮ እነዚህን አገልጋዮቹን አድኖአል፤ እነርሱ በአምላካቸው ተማምነው ለእርሱ ካልሆነ በቀር ለሌሎች አማልክት አንሰግድም በማለት የንጉሡን ትእዛዝ በማፍረስ ሕይወታቸውን በአደጋ ላይ ጥለውት ነበር።
የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ተርፈው ከስደት ከተመለሱት ሕዝብ ጋር ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ቃልና፥ እግዚአብሔር የላከው ስለ ሆነ በነቢዩ ሐጌ አማካይነት ለተላከው መልእክት ታዛዦች ሆኑ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ።
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም በጥሞና አዳመጣቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩና ስሙንም የሚያከብሩ ሰዎች ለተግባራቸው መታሰቢያ በመጽሐፍ ተጻፈ።
ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤