“በተራቡም ጊዜ ምግብን ከሰማይ ሰጠሃቸው፤ በተጠሙም ጊዜ ውሃን ከአለት አፈለቅህላቸው፤ ለእነርሱ ልትሰጣቸው ቃል የገባህላቸውንም ምድር በቊጥጥራቸው ሥር ያደርጉ ዘንድ አዘዝካቸው።
ኢሳይያስ 48:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በምድረ በዳ በመራቸው ጊዜ ውሃ አልጠማቸውም፤ ይልቁንስ ውሃ ከአለት እንዲፈልቅላቸው አደረገ። አለቱን ከፍሎ ውሃ አጐረፈላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳ ሲመራቸው አልተጠሙም ነበር፤ ውሃ ከዐለት አፈለቀላቸው፤ ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃውም በኀይል ፈልቆ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድረ በዳ በኩል በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፥ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድረ በዳም በተጠሙ ጊዜ፥ ውኃን ከዓለቱ ውስጥ ያፈልቅላቸው ነበር፤ ዓለቱም ተሰነጠቀ፤ ውኃውም ይፈስስላቸው ነበር፤ ሕዝቤም ይጠጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድረ በዳ በኩል በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፥ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፥ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ። |
“በተራቡም ጊዜ ምግብን ከሰማይ ሰጠሃቸው፤ በተጠሙም ጊዜ ውሃን ከአለት አፈለቅህላቸው፤ ለእነርሱ ልትሰጣቸው ቃል የገባህላቸውንም ምድር በቊጥጥራቸው ሥር ያደርጉ ዘንድ አዘዝካቸው።
እነሆ፥ እኔ በሲና ተራራ በአለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ አንተም አለቱን ምታው፤ ሕዝቡም የሚጠጡት ውሃ ከውስጡ ይፈልቃል፤” ሙሴም በእስራኤል አለቆች ፊት እንደዚሁ አደረገ።
መራብና መጠማትም አይደርስባቸውም፤ የሚያቃጥል ነፋስ ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም፤ ይህም የሚሆነው የሚራራላቸው እርሱ የውሃ ምንጭ ወደሚገኝበት ቦታ ስለሚመራቸው ነው።
እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”