ኢሳይያስ 46:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከማሕፀን ጀምሬ የጠበቅኋችሁና ከልደት ጀምሬ የረዳኋችሁ የያዕቆብ ልጆች የሆናችሁ፥ የእስራኤል ቅሪቶች! አድምጡኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ ከተፀነሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የያዝኋችሁ፣ ከተወለዳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የተሸከምኋችሁ ስሙኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁን፥ ስሙኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከማኅፀንም ጀምሮ የተሸከምኋችሁ፥ ከሕፃንነትም ጀምሮ ያስተማርኋችሁ፥ ስሙኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁ፥ ስሙኝ። |
“ ‘እኔ እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ያደረግኹትንና ንስር ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ እንደምትሸከም እኔም እናንተን እስከዚህ ስፍራ እንዴት ወደ እኔ እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል፤
በዚያን ጊዜ ከጥፋት የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ፥ ጥቃት ባደረሱባቸው በአሦራውያን ላይ አይተማመኑም፤ በዚህ ፈንታ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይተማመናሉ።
ምንም እንኳ የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ቢሆንም ከእነርሱ መካከል የሚድኑት የተረፉት ብቻ ናቸው፤ ለሕዝቡ ጥፋት ተገቢ የሆነ እውነተኛ ፍርድ ተዘጋጅቶአል።
በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።
የአሦር ንጉሥ ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ስለሚተርፉት እባክህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”
በእስራኤል ስም የምትጠሩ፥ ከይሁዳ ወገን የሆናችሁ፥ እናንተ የያዕቆብ ልጆች! ይህን ስሙ። እናንተ በታማኝነትና በእውነት ሳይሆን፥ የእስራኤልን አምላክ እናመልካለን ትላላችሁ፤ በእግዚአብሔር ስምም ትምላላችሁ።
በችግራቸው ጊዜ ሁሉ ያዳናቸው በመልእክተኛ ወይም በመልአክ አማካይነት ሳይሆን እርሱ በመካከላቸው በመገኘት ነው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ታደጋቸው፤ እርሱም በቀድሞ ዘመናት ሁሉ አንሥቶ ልጁን እንደሚሸከም ሰው ተንከባከባቸው።
እናንተ ወደዚህ ቦታ እስክትመጡ ድረስ አንድ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳው እንደ ተንከባከባችሁ አይታችኋል።’