እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አድነን! ከመንግሥታት መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግንሃለን፤ ቅዱስ ስምህንም እናከብራለን።
ኢሳይያስ 43:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከእናንተ ጋር ስለ ሆንኩ አትፍሩ፤ ከምሥራቅም ከምዕራብም እናንተንና ልጆቻችሁን ሰብስቤ አመጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፥ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፤ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፥ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ። |
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አድነን! ከመንግሥታት መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግንሃለን፤ ቅዱስ ስምህንም እናከብራለን።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።
በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።
ቀና ብለሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ ልጆችሽ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እንዲህ እላለሁ፦ ‘ሁሉንም እንደ ልብስ ትለብሺአቸዋለሽ፤ ሙሽራ በጌጣጌጥ እንደምታጌጥ አንቺም በእነርሱ ታጌጪአለሽ።’
ልጆቻቸው በወገኖች ዘንድ፥ የልጅ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር የተባረኩ ዘሮች መሆናቸውን ያውቃሉ።
የጦር ዕቅድንም አውጡ፤ ነገር ግን እናንተ እንዳሰባችሁት አይሳካላችሁም፤ የፈለጋችሁትን ያኽል ተናገሩ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምክራችሁ አይጸናም።
በዚህ ፈንታ፥ የእስራኤልን ሕዝብ ከሰሜን ምድርና ተበታትነው ከነበሩባቸው ሌሎች አገሮች ሰብስቤ ባመጣኋቸው በእኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም ይምላሉ፤ ከዚያም በኋላ በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።”
በእርግጥ እላችኋለሁ ታገኙኛላችሁ፤ እኔም ወደ ምድራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ እናንተን ከበተንኩበት ከየትኛውም አገርና ከየትኛውም ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ እኔ እናንተን ነቅዬ እንድትሰደዱ ከማድረጌ በፊት ወደ ነበራችሁበት ምድር መልሼ አመጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እስራኤልና ይሁዳ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱም በአንድነት በስተሰሜን ካለው አገር ከምርኮ ይመለሳሉ፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የዘለዓለም ርስት አድርጌ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ተመልሰው ይገባሉ።”
ከምትሰሙትም የጒምጒምታ ወሬ የተነሣ በመፍራት ወኔአችሁ አይቀዝቅዝ፤ በየዓመቱ ልዩ ልዩ የጒምጒምታ ወሬ ይነዛል፤ በምድሪቱ ላይ አንዱ ንጉሥ ሌላውን እንደሚወጋ የሚገልጥ የዐመፅ ጒምጒምታ ወሬ ይሰማል።
እነሆ አሁን ከተሸጡባቸው ስፍራዎች አነሣሥቼ እንዲወጡ አደርጋለሁ፤ በእነርሱ ላይ የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ በእናንተ ላይ መልሼ አመጣባችኋለሁ።
“የእስራኤል ሕዝብ! በጎች በበረት፥ የበግ መንጋም በማሰማሪያ ቦታ እንደሚሰበሰብ በእርግጥ ከእስራኤል ሕዝብ የተረፉትን በአንድነት እሰበስባለሁ፤ ምድሪቱም በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር።
በዚህ መንጋ ውስጥ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት ይገባኛል፤ እነርሱ ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ ይሆናል።