እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው።
ኢሳይያስ 40:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቦች እንደ አንድ የውሃ ጠብታ ናቸው፤ በሚዛንም ላይ እንዳለ ዐቧራ ናቸው፤ ደሴቶችም በእርሱ ዘንድ እንደ ትቢያ የቀለሉ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ አሕዛብ በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው፤ በሚዛን ላይ እንዳለ ትቢያ ይቈጠራሉ፤ ደሴቶችንም እንደ ደቃቅ ዐፈር ይመዝናቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፤ እንደ ሚዛንም ውልብልቢት ተቈጥረዋል፤ እንደ ኢምንትም ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፥ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል። |
እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው።
ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤ ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።
በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።
ሕዝቦች እንደ ኀይለኛ ውሃ ድምፅ ያሰማሉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲገሥጻቸው በተራራ ላይ ገለባዎች በነፋስ እንደሚበተኑና በዐውሎ ነፋስም ዐቧራ እንደሚበተን ርቀው ይሸሻሉ።
ኢየሩሳሌም ሆይ! በአንቺ ላይ በጠላትነት የሚነሡ የጠላት ሠራዊት ሁሉ እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፤ እጅግ የሚያስፈሩ ሠራዊቶቻቸውም ሳይታሰቡ በድንገት በነፋስ እንደሚወሰድ ገለባ ይሆናሉ።
እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።
“በደሴቶች የሚኖሩ ሕዝቦች እኔ ያደረግኹትን ሁሉ አይተዋል፤ ስለዚህም እጅግ ደንግጠው ተንቀጥቅጠዋል፤ በአንድነትም ተሰብስበው ወደ እኔ መጥተዋል።
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።
ከዚያ በኋላ በባሕር ጠረፍ ባሉት አገሮች ላይ አደጋ ጥሎ ከእነርሱ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ የጦር መሪ ድል ስለሚነሣው የትዕቢቱ ፍጻሜ ይሆናል፤ በእርግጥም በትዕቢት የተናገረው ስድብ ሁሉ በእርሱ ላይ ይፈጸማል።
ከሕዝብ መካከል ተባረህ መኖሪያህ ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ ይህም የሚሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ነው።”
በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።
በምድራቸው ያሉትን ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በማጥፋቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በባሕር ጠረፍና በደሴቶች የሚኖሩ መንግሥታት ሁሉ በያሉበት ለእርሱ ይሰግዳሉ።