ኢሳይያስ 37:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እርሱ ወደዚህች ከተማ ሳይገባ በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ ወደዚህች ከተማም አይገባም” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፤ ወደዚችም ከተማ አይመጣም፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጣበትም መንገድ በዚያ ይመለሳል፤ ወደዚህም ከተማ አይመጣም ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፥ ወደዚችም ከተማ አይመጣም ይላል እግዚአብሔር። |
በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”