ከተሞችን ደምስሶ ዓለምን ወደ ምድረ በዳነት የለወጣት ሰው ይህ ነውን? እስረኞች ነጻ እንዳይለቀቁና ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ የሚያደርግ እርሱ አልነበረምን?”
ኢሳይያስ 37:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሦር ነገሥታት አንድን አገር ለማጥፋት በሚፈልጉበት ጊዜ ሁሉ እንዴት እንደሚያወድሙአት ሰምተሃል፤ ታዲያ፥ አንተስ ከዚህ የምታመልጥ ይመስልሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ የአሦር ነገሥታት በአገሮች ሁሉ ላይ ያደረጉትን፣ ፈጽሞም እንዳጠፏቸው ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን፥ እንዴትስ እንዳጠፉአቸው ሰምተሃል፤ አንተስ ትድናለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን እንዴትስ እንዳጠፉአቸው አልሰማህምን? አንተስ ትድናለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን፥ እንዴትስ እንዳጠፉአቸው ሰምተሃል፥ እንተስ ትድናለህን? |
ከተሞችን ደምስሶ ዓለምን ወደ ምድረ በዳነት የለወጣት ሰው ይህ ነውን? እስረኞች ነጻ እንዳይለቀቁና ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ የሚያደርግ እርሱ አልነበረምን?”
ሕዝቅያስ ‘በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱ ያድነናል፤ ከተማችንም በአሦራውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል’ እያለ የሚያግባባችሁን አትስሙት።
ክፉኛ የተጐዳሽ ስለ ሆነ ቊስልሽን ሊፈውስ የሚችል ነገር የለም፤ ማለቂያ ከሌለው ከአንቺ የጭካኔ ድርጊት ያመለጠ ሰው ስለሌለ ስለ አንቺ የሚሰሙ ሁሉ በአንቺ መውደቅ ያጨበጭባሉ።