ከዚያን በኋላ በገዛ እጃቸው በሠሩት መሠዊያ መታመናቸው ይቀራል፤ እንዲሁም የእጃቸው ሥራ በሆኑት በአሼራ ምስልና ዕጣን ሊያጥኑባቸው በሠሩአቸው መሠዊያዎች መተማመናቸውን ይተዋሉ።
ኢሳይያስ 31:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኃጢአተኛ እጃችሁ ከብርና ከወርቅ የሠራችኋቸውን ጣዖቶቻችሁን ሁሉ አሽቀንጥራችሁ የምትጥሉበት ጊዜ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን በኀጢአት የተሞላ እጃችሁ የሠራቸውን የወርቅና የብር ጣዖቶች ሁላችሁም ትጥላላችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው ለኃጢአት የሠሩላቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው የሠሩአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው ለኃጢአት የሠሩላቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉ። |
ከዚያን በኋላ በገዛ እጃቸው በሠሩት መሠዊያ መታመናቸው ይቀራል፤ እንዲሁም የእጃቸው ሥራ በሆኑት በአሼራ ምስልና ዕጣን ሊያጥኑባቸው በሠሩአቸው መሠዊያዎች መተማመናቸውን ይተዋሉ።
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እኔ ከጣዖቶች ጋር ምን ግንኙነት አለኝ? ለጸሎታችሁ መልስ የምሰጥና የምንንከባከባችሁ እኔ ነኝ፤ እኔ ዘወትር ለምለም ሆኖ እንደሚታይ የጥድ ዛፍ ነኝ፤ ፍሬያማ የምትሆኑትም በእኔ አማካይነት ነው።”
ጣዖቶቻቸውን በእሳት አቃጥል፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ የራስህ ንብረት አድርገህ ለመውሰድ ልብህ አይመኝ፤ ይህን ብታደርግ ወጥመድ ይሆንብሃል፤ እግዚአብሔርም አምልኮ ጣዖትን ስለሚጠላ ብርቱ ጥፋትን ያስከትልብሃል።