ኢሳይያስ 30:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ክቡር ድምፁን እንዲሰሙ ያደርጋል። በኀይለኛ ቊጣው፥ በሚያቃጥል የእሳት ነበልባል፥ በመብረቅ፥ በወጀብና በጠጣር በረዶ የሚወርደው ኀይለኛ ቅጣቱ እንዲታይ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በሚነድድ ቍጣና በሚባላ እሳት፣ በወጀብና በነጐድጓድ፣ በበረዶም ድንጋይ፣ ግርማ የተሞላበትን ድምፁን ሰዎች እንዲሰሙ አድርጎ ያሰማል፤ ክንዱም ስትወርድ ያሳያቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድ ቁጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በበረዶ፥ ጠጠርም ይገልጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የድምፁን ክብር ያሰማል፤ የክንዱንም መፈራት፥ በጽኑ ቍጣና በምትበላ እሳት፥ በወጀብም፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በበረዶም ድንጋይ ይገልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድድ ቍጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል በዐውሎ ነፋስም በወጨፎም በበረዶ ጠጠርም ይገልጣል። |
አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በሥልጣንህ እንደ ድንጋይ ጸጥ አሉ።
ስለዚህ ሙሴ በትሩን አንሥቶ ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና በረዶ መብረቅም ወደ ምድር አወረደ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር በግብጽ ምድር ላይ በረዶን አዘነበ።
እግዚአብሔር በዚህና በዚያ ከሚራወጥ የመብረቅ ብልጭልጭታ ጋር ከባድ የበረዶ ዝናብ አወረደ፤ ይህም ዐይነቱ የበረዶ ዝናብ በግብጽ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነበር።
ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ በግዙፉ ሠራዊቱ ላይ የሚያመነምን በሽታ ይልክበታል፤ በሰውነቱም ውስጥ እንደ እሳት የሚያቃጥል ትኲሳት ይልክበታል።
እኔ የሠራዊት አምላክ በዖሬብ አለት አጠገብ በምድያማውያን ላይ እንዳደረግሁት አሦራውያንን የምቀጣበት ጅራፍ ባሕሩን በበትሬ መትቼ ግብጻውያንን እንደቀጣሁ አሦራውያንን እቀጣለሁ። በግብጽ ላይ በትሬን እንዳነሣሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይም አነሣለሁ።
እነሆ፥ ጌታ እንደ በረዶ ወጨፎ፥ እንደሚያጠፋ ዐውሎ ነፋስና እንደሚያጥለቀልቅ ኀይለኛ የውሃ ጐርፍ የሆነ አንድ ጠንካራና ኀያል ሰው አለው። ይህም ሰው በሥልጣኑ ወደ ምድር አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።
የሠራዊት ጌታ አምላክ ነጐድጓድን፥ የመሬት መናወጥን፥ ታላቅ ድምፅን፥ ዐውሎ ነፋስን፥ ሞገድንና የሚባላ የእሳት ነበልባልን በጠላቶችሽ ላይ በመላክ አንቺን ይታደግሻል።
እናንተ ግን ደስ ይላችኋል፤ በተቀደሰ በዓል ምሽት እንደምትዘምሩት ትዘምራላችሁ፤ የእስራኤል አምባ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዋሽንት እየነፉ እንደሚዘምሩት ሰዎች ትደሰታላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “አንበሳ በገደለው እንስሳ ላይ በሚያገሣበት ጊዜ እረኞች ተጠራርተው የቱንም ያኽል ቢጮኹ የእነርሱ ጩኸት ምንም እንደማያስፈራው እኔም የሠራዊት አምላክ የጽዮንን ተራራና ኰረብቶቿን ለመከላከል የሚያግደኝ የለም።
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።
እግዚአብሔር በኃይሉና በሥልጣኑ እንዲህ ሲል ማለ፦ “ከእንግዲህ ወዲያ እህልሽን ጠላቶችሽ እንዲበሉት አላደርግም፤ የደከምሽበትን አዲስ የወይን ጠጅሽንም ባዕዳን እንዲጠጡት አላደርግም።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ በሕዝቦች ሁሉ ላይ በየተራ ጥፋት ይመጣል፤ በምድር ዳርቻዎች ሁሉ ላይ ታላቅ ዐውሎ ነፋስ ይነሣል።
ኪሩቤል በክንፎቻቸው የሚያሰሙት ድምፅ በውጪ በኩል ባለው አደባባይ እንኳ ይሰማ ነበር፤ ድምፁም ሁሉን የሚችል አምላክ ድምፅ ይመስል ነበር።
ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኢየሩሳሌምን ቅጽር ለማጥፋት በቊጣዬ ዐውሎ ነፋስ እንዲነሣ አደርጋለሁ። ዶፍ ዝናብና የበረዶ ናዳ ይወርዳል።
እንደ ሠረገላ ድምፅ እያሰሙ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘላሉ፤ ገለባን እንደሚያቃጥል እሳትም፥ ሁሉን ነገር ያቃጥላሉ፤ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ብርቱ ሠራዊት በሰልፍ ይተማሉ።
ስለዚህ በራባ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል፤ ከዚህ በኋላ በጦርነቱ ቀን ጩኸትና ሁካታ ይበዛል፤ ጦርነቱም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይፈጥናል፤
በዚያን ጊዜ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥና፥ ውሃም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ታች እንደሚወርድ እንዲሁም ተራራዎች ከእርሱ ሥር ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይከፈታሉ።
ከሰማይ የሚገለጠውም በሚንበለበል እሳት ነው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይቀጣቸዋል።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ሠራዊት ፊት አሞራውያን በድንጋጤ እንዲሸበሩ አደረገ፤ እስራኤላውያንም እነርሱን በገባዖን ዐረዱአቸው፤ የቀሩትንም በቤትሖሮን በኩል እስከ ተራራው መተላለፊያ ቊልቊለት እስከ ዐዜቃና እስከ ማቄዳ ድረስ አሳደዱአቸው።
አሞራውያን በመተላለፊያው ቊልቊለት ከእስራኤላውያን ሠራዊት በሚሸሹበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር እስከ ዐዜቃ ድረስ ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ ስለዚህም እስራኤላውያን ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶው ድንጋይ የሞቱት እጅግ ብዙዎች ነበሩ።
በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በማቅረብ ላይ ሳለ ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ለመውጋት ዘመቱ፤ ነገር ግን በዚያች ቀን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ከፍተኛ ነጐድጓድ አንጐድጒዶ አርበደበዳቸው፤ እነርሱም ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ።