ኢሳይያስ 30:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ፈንታ በፈጣን ፈረሶች ላይ ተቀምጣችሁ ከጠላቶቻችሁ እጅ ለማምለጥ ታቅዳላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ‘ፈረሶቻችን እጅግ ፈጣኖች ናቸው’ ትሉ ይሆናል፤ ነገር ግን አሳዳጆቻችሁ ከእናንተ የፈጠኑ ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ‘አይሆንም፣ በፈረስ እንሸሻለን’ አላችሁ፤ ስለዚህ ትሸሻላችሁ! ደግሞም፣ ‘በፈጣን ፈረስ እናመልጣለን’ አላችሁ፤ ስለዚህ አሳዳጆቻችሁም ፈጣን ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን፦ “በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም” አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፦ “በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን” አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዷችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን፥ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፤ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን፦ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፥ ደግሞም፦ በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ። |
ምድራቸው በብርና በወርቅ ስለ ተሞላች፥ ሀብታቸው ከመጠን በላይ ነው፤ አገራቸው በፈረሶች የተሞላች ሆናለች፤ ሠረገሎቻቸውም እጅግ ብዙ ናቸው።
ብዙ ፈረሶች፥ ሠረገሎችና ወታደሮች ባሉት ብርቱ በሆነው በግብጽ ሠራዊት ተማምነው ርዳታ ለማግኘት ወደ ግብጽ ለሚወርዱ ወዮላቸው! ነገር ግን የእስራኤልን ቅዱስ ርዳታ አይለምኑም፤ መመሪያውንም አይቀበሉም።
ግብጻውያን ሰዎች ናቸው እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ ለባሾች እንጂ የተለዩ መናፍስት አይደሉም፤ እግዚአብሔር በቊጣው በሚነሣበት ጊዜ ይህ የሌሎች ረዳት የሆነው መንግሥት ይደናቀፋል፤ እርሱ ይረዳው የነበረውም መንግሥት ተንኰታኲቶ ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ይጠፋሉ።
ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ በሌሊት ከከተማይቱ ወጥተው ለማምለጥ ሞከሩ፤ በቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ በኩል አድርገው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው መውጫ በር አቋርጠው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ አመለጡ።
“እነሆ የጠላት ሠራዊት እንደ ደመና አንዣቦአል፤ የጦር ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ፈጣኖች ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይበልጥ ይበራሉ፤ ለእኛ ወዮልን! ጠፍተናል!
የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ከበው ሳለ ወታደሮቹ በሌሊት አምልጠው ነበር፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ በሚወስደው መንገድ በኩል በማለፍ ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው በቅጽር በር ወጥተው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ፤
እግዚአብሔርን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “መድረኮቹ እስኪናወጡ ድረስ የቤተ መቅደሱን ጒልላት ምታ፤ ሰባብረህም በሰዎቹ አናት ላይ እንዲደረመስ አድርግ፤ ከዚያ የተረፉትንም እኔ በሰይፍ እጨርሳቸዋለሁ፤ ማንም መሸሽ አይችልም፤ ማንም ሊያመልጥ አይችልም።
“ፈረሶቻቸው ከነብር ይበልጥ ፈጣኖች፥ ከማታ ተኲላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም እየጋለቡ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ነጥቀው ለመብላትም እንደ ንስር ይበራሉ።
“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤