ኢሳይያስ 29:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካለችበት ከጥልቁ ጒድጓድ ትናገራለች፤ ከታች ከትቢያ ውስጥ ንግግርዋ ይመጣል፤ ድምፅዋም እንደ ምትሐት ከምድረ በዳ ይወጣል፤ ከአዋራ ውስጥም ዝቅ ያለ ድምፅዋ ይሰማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ ንግግርሽ ከትቢያ እየተጕተመተመ ይወጣል፤ ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዋረጃለሽ፥ መሬት ላይ ተደፍተሽ ትናገሪያለሽ፥ ቃልሽም በዝግታ ከአፈር ይወጣል፤ ድምጽሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ድምፅ ይሆናል፥ ንግግርሽም ከአፈር በሹክሹክታ ይወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገርሽም በምድር ውስጥ ይሰጥማል፤ ቃልሽም ከምድር በታች እንደሚናገር ይሆናል፤ ትደክሚያለሽ፤ ቃልሽም በምድር ውስጥ ዝቅ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዋረጅማለሽ፥ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፥ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፥ ድምጽሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መንፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፥ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ ይጮኸል። |
ኢየሩሳሌም ተሰናክላ በመንገዳገድ ላይ ናት፤ ይሁዳም ልትወድቅ ተቃርባለች፤ ምክንያቱም የሚናገሩትም ሆነ የሚሠሩት ሁሉ እግዚአብሔርን በመፈታተን ስለ ሆነ ክብሩን አቃለዋል።
የመከራውንም ጽዋ ‘አጐንብሺና በጀርባሽ እንራመድብሽ’ ለሚሉና አንቺን ለሚያሠቃዩ ሰዎች በእጃቸው እሰጣለሁ፤ አንቺም እነርሱ ይራመዱብሽ ዘንድ ጀርባሽን እንደ መሬትና እንደ መንገድ አድርገሻል።”
ምርኮኛይቱ ኢየሩሳሌም ሆይ! ተነሥተሽ ትቢያሽን አራግፊ፤ በዙፋን ላይም ተቀመጪ፤ እናንተም የጽዮን ምርኮኞች ሆይ! የታሰራችሁበትን ሰንሰለት ከአንገታችሁ ፍቱ።
“በመንተባተብ የሚቀባጥሩትን ሟርተኞችንና የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ” እያሉ የሚሰብኩአችሁ ወገኖች አሉ፤ ታዲያ፥ ስለ ሕያዋን ሙታንን ከመጠየቅ ይልቅ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን?
አደፍዋ በቀሚስዋ ላይ ይታያል፤ ለወደፊት ምን እንደሚደርስባት አላሰበችም፤ አወዳደቅዋ የሚያሰቅቅ ነው፤ የሚያጽናናት ከቶ የለም፤ ጠላቶችዋ ድል ስላደረግዋት፥ መከራዋን እንዲመለከትላት ወደ እግዚአብሔር ጸለየች።