ጢሮስ ሰባ ዓመት ያኽል ተረስታ የምትኖርበት ጊዜ ይመጣል፤ ይህም የአንድ ንጉሥ ዕድሜ ነው፤ እነዚያ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ጢሮስ እንደ ዘማዊት ሴት እንዲህ ተብሎ ቅኔ የሚነገርባት ትሆናለች፦
ኢሳይያስ 23:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰባ ዓመት በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞ የንግድ ሥራዋ እንድትመለስ ያደርጋታል፤ በምድር ላይ ከሚገኙ መንግሥታት ሁሉ ጋር ታመነዝራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባው ዓመት ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞው የግልሙትና ሥራዋ ተመልሳ፣ በምድር ላይ ካሉት የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋራ በንግዷ ትገለሙታለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰባ ዓመትም በኋላ ጌታ ጢሮስን ይጎበኛታል፥ ወደ ዋጋዋም ትመለሳለች፥ ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን በይቅርታ ይጐበኛታል፤ ወደ ጥንቷም ትመለሳለች፤ ደግሞም ለዓለም መንግሥታት ሁሉ መናገሻና መናገጃ ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጎበኛታል፥ ወደ ዋጋዋም ትመለሳለች፥ ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች። |
ጢሮስ ሰባ ዓመት ያኽል ተረስታ የምትኖርበት ጊዜ ይመጣል፤ ይህም የአንድ ንጉሥ ዕድሜ ነው፤ እነዚያ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ጢሮስ እንደ ዘማዊት ሴት እንዲህ ተብሎ ቅኔ የሚነገርባት ትሆናለች፦
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በባቢሎን የምትኖሩበት ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ እንደገና እናንተን በምሕረት እጐበኛለሁ፤ ወደ አገራችሁ እንድመልሳችሁ የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤
በዚህ ዐይነት በየአውራ መንገዱ ዳር የጣዖት ማምለኪያ ቦታዎችን ሠርተሽ ውበትሽን አረከስሽ፤ ለመጣው ሁሉ ሰውነትሽን አሳልፈሽ እየሰጠሽ በየቀኑ አመንዝራነትሽን አበዛሽ።
በየመንገዱ ዳር መድረክሽን ትሠሪአለሽ፤ በየአደባባዩም የጣዖት ማምለኪያ ቦታሽን ታዘጋጂአለሽ፤ ሆኖም እንደ ተራ አመንዝራ ሴት ገንዘብ ለመሰብሰብ እንኳ አልፈለግሽም።
ምስሎችዋ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለመቅደስዋ አመንዝሮች የተከፈለውም ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ፤ ጣዖቶችዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፤ ሰማርያ እነዚህን ምስሎች የሰበሰበቻቸው የዝሙት ዋጋ መቀበያ ለማድረግ ነበር፤ አሁንም ጠላቶችዋ የዝሙት መጠቀሚያ ያደርጉአቸዋል።”
የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።
ይህም የሆነው ገደብ በሌለው የአምንዝራይቱ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርስዋ በመተት እመቤትነትና በቊንጅናዋ የምታታልልና መንግሥታትን በዝሙትዋ፥ ሕዝቦችን በጥንቈላዋ የምትማርክ ነች።
እግዚአብሔር አምላካቸው ስለሚንከባከባቸውና ንብረታቸውን ስለሚመልስላቸው ከብቶቻቸውን ያሰማሩበት ዘንድ የባሕሩ ዳር ከይሁዳ ሕዝብ ለተረፉት ርስት ይሆናል፤ በየምሽቱም በአስቀሎና ቤቶች ያድራሉ።
እግዚአብሔር ዝሙትን ስለሚጠላ በዚህ ተግባር የተገኘ ገንዘብ የስእለትን መፈጸም የሚያመለክት ስጦታ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር አምላክህ ቤት አይግባ።
በዐደራ የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ መንጋውን የምትጠብቁትም በግድ ሳይሆን እግዚአብሔር በሚፈልገው ዐይነት፥ በፈቃደኛነት ይሁን፤ ለገንዘብ በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ፍላጎት ይሁን።
ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው፤ ምድርን በአመንዝራነትዋ ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ በፍርድ ቀጥቶአታል፤ እርስዋን በመቅጣትም የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።”