ኢሳይያስ 23:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንግሥታትን በማናወጥ የእግዚአብሔር ኀይል እስከ ባሕር ማዶ ደርሶአል፤ በከነዓንም ምድርም ያሉ ምሽጎች እንዲፈርሱ አዞአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እጁን በባሕር ላይ ዘረጋ፤ መንግሥታቷንም አስደነገጠ፤ የከነዓንም ምሽጎች እንዲፈርሱ፣ ትእዛዝ ሰጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጁን በባሕር ላይ ዘረግቶ መንግሥታትንም አናውጧል፤ የከነዓንም ምሽጎች እንዲፈርሱ ጌታ አዟል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሥታቱን ያበሳጨቻቸው የባሕር ሰዎች እጃቸው ትደክማለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የከነዓንን ኀይል ያጠፉ ዘንድ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባሕር ላይ እጁን ዘረጋ መንግሥታትንም አናወጠ፥ ምሽጎችዋንም ያጠፉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለ ከነዓን አገር አዘዘ። |
ሙሴ እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ባሕሩን ወደ ኋላ መለሰው፤ ነፋሱም ሌሊቱን ሙሉ በመንፈሱ፥ ባሕሩን ወደ ደረቅ ምድር ለወጠው፤ ውሃውም ከሁለት ተከፈለ፤
ሀብታቸውን ዘርፈውና መዝብረው ሕዝቡን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንዲረግጡ በከሐዲውና ቊጣዬንም ባነሣሣው ሕዝብ ላይ አሦራውያንን አስነሥቼ እልካቸዋለሁ።”
እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚመጣበት ጊዜ ከቊጣውና ከአስፈሪ ግርማው ለማምለጥ በአለት ዋሻና በመሬት ንቃቃት ውስጥ ለመሸሸግ ይሞክራሉ።
ከተሞች ፈርሰው ባድማ እንዲሆኑ አድርገሃል፤ ምሽጎቻቸውንም አፈራርሰሃል፤ ጠላቶቻችን የሠሩአቸው ቤተ መንግሥቶች እንዳልነበሩ ሆነዋል፤ እስከ ዘለዓለምም እንደገና አይሠሩም።
እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ በጣም ተቈጥቶአል፤ በኀያልነቱም ይቀጣቸዋል፤ ተራራዎች ይናወጣሉ፤ የሞቱ ሰዎችም አስከሬን እንደ ጥራጊ በየመንገዱ ዳር ይወድቃል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ አይበርድም፤ እንደገናም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶአል።
“እኔ በመጣሁ ጊዜ ማንም ሰው አለመኖሩ ለምንድን ነው? በጠራሁም ጊዜ ማንም ሰው መልስ ያልሰጠኝ ለምንድን ነው? እኔ ለመታደግ አልችልምን? ለማዳንስ ኀይል የለኝምን? በተግሣጼ ብቻ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ወደ ምድረ በዳነት እለውጣለሁ፤ ዓሣዎቻቸውም ውሃ ከማጣት የተነሣ ሞተው ይበሰብሳሉ።
ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር የሰጠሁትን ሥራ ሳይፈጽም እንዴት ማረፍ ይችላል? እኔ በአስቀሎናና በጠረፎችዋ በሚኖሩ ሕዝብ ላይ አደጋ እንዲጥል አዝዤዋለሁ።”
በፈረሶቻቸው ኮቴ የሚነሣው አቧራ እንደ ደመና ሆኖ ይሸፍንሻል፤ እርሱ ወደ ቅጥር በሮችሽ በሚገባበት ጊዜ ከፈረሰኛው፥ ከሠረገላውና ከመንኰራኲሩ የሚሰማው ድምፅ ተጥሳ እንደሚገባባት ከተማ ቅጥሮችሽን ያናጋል።
የከተማሽን የቅጽር ግንቦች ያፈራርሳሉ፤ የዘብ መጠበቂያ ግንብሽን ይሰባብራሉ፤ ዐፈሩን ሁሉ ጠራርጌ በማጥፋት አለቱ ብቻ አግጥጦ እንዲቀር አደርጋለሁ፤
እኔ ያን ዛፍ ወደ ሙታን ዓለም እንዲወርድ በማደርግበት ጊዜ አወዳደቁ የሚያሰማው ድምፅ ሕዝቦችን ሁሉ ያንቀጠቅጣል፤ ወደ ሙታን ዓለም የወረዱ የዔደን ዛፎችና የጥሩ መስኖ ውሃ የሚጠጡ የተመረጡ የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እርሱ ወደ ሙታን ዓለም በመውረዱ ደስ ይላቸዋል፤
እግዚአብሔር ስለ አሦራውያን የሰጠው ፍርድ እንዲህ የሚል ነው፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስማችሁን የሚያስጠራ ተተኪ ዘር አይኖራችሁም፤ በአማልክታችሁ ቤተ መቅደስ የሚገኙትን የተቀረጹ ምስሎችንና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶችን አጠፋለሁ፤ እናንተም ዋጋ ቢሶች ስለ ሆናችሁ የመቃብር ጒድጓድ እምስላችኋለሁ።”
በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር የሚገኘው ማሰሮ ሁሉ ለሠራዊት አምላክ የተለየ ይሆናል፤ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ሰዎች ሁሉ በማሰሮዎቹ ጥቂቱን የመሥዋዕቱን ሥጋ ያበስሉባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ የሚነግድ ማንም ሰው አይኖርም።