ኢሳይያስ 23:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተርሴስ ሕዝብ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ ወደብ ስለሌላችሁ ልክ በአባይ ወንዝ ዳር እንደሚደረገው ምድራችሁን እረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተርሴስ ልጅ ሆይ፤ ከእንግዲህ የሚከለክልሽ የለምና እንደ አባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተርሴስ ልጅ ሆይ፥ የሚከለክልሽ የለምና እንደ ዓባይ ወንዝ በምድርሽ ላይ ፍሰሺ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርህን እረስ፤ እንግዲህ መርከቦች ከኬልቀዶን አይመጡምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተርሴስ ልጅ ሆይ፥ የሚከለክልሽ የለምና እንደ አባይ ወንዝ በአገርሽ ላይ ጎርፈሽ እለፊ። |
ይህንማ ያቀደው የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱም ይህን ያቀደው ባደረጉት ነገር መታበያቸውን እንዲተዉ ለማድረግና የተከበሩትንም ሰዎች ለማዋረድ ብሎ ነው።
የኢየሩሳሌም ክብር ሁሉ ጠፍቶአል፤ መሪዎችዋ መሰማሪያ እንዳጡ ዋልያዎች ናቸው፤ አሳዳጆቻቸው ሲያባርሩአቸው ጒልበታቸው እስኪዝል ድረስ ሸሹ።
በዚያን ጊዜ፥ የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ ኀይላቸውንም እንዳልነበረ አደርጋለሁ፤ ሠረገላ ነጂዎችን ከነሠረገሎቻቸው እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቻቸው ያልቃሉ፤ ፈረሰኞቻቸውም እርስ በርሳቸው ይጋደላሉ፤
ሳኦልም ሳሙኤል በተናገረው ቃል ደንግጦ በመዝለፍለፍ ወደቀ፤ በመሬት ላይም ተዘረረ፤ ቀኑንና ሌሊቱን ሁሉ እህል ስላልቀመሰ ድካም ተሰምቶት ነበር።