“ስለዚህ ወደዚህ የላከኝ ራሱ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ለፈርዖን እንደ መካሪ አባት፥ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታና የመላው ግብጽ አገር ገዢ አደረገኝ።
ኢሳይያስ 22:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንተ የነበረውን የማዕርግ ልብስ አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህንም እሰጠዋለሁ፤ የአንተ የነበረውንም ሥልጣን ሁሉ ለእርሱ አስረክባለሁ፤ እርሱ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሕዝቦች እንደ አባት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጎናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፥ በመታጠቅያህም አስታጥቀዋለሁ፥ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጐናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፤ አክሊልህንም እሰጠዋለሁ፤ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩና በይሁዳም ለሚኖሩ አባት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጎናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፥ በመታጠቅያህም አስታጥቀዋለሁ፥ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል። |
“ስለዚህ ወደዚህ የላከኝ ራሱ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ለፈርዖን እንደ መካሪ አባት፥ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታና የመላው ግብጽ አገር ገዢ አደረገኝ።
መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፥ ሐምራዊ ካባ ደርቦና ውብ የሆነ የወርቅ አክሊል ደፍቶ ከቤተ መንግሥት ብቅ አለ፤ በሱሳም ከተማ የሆታና የእልልታ ድምፅ አስተጋባ።
ንጉሡም የራሱ ማኅተም ያለበትን፥ ከሃማን ጣት ወልቆ እንዲመለስ የተደረገውን ቀለበት ለመርዶክዮስ ሰጠው፤ አስቴርም መርዶክዮስን በሃማን ሀብትና ንብረት ላይ ኀላፊ አድርጋ ሾመችው።