ኢሳይያስ 19:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንዞቹ ይገማሉ፤ የግብጽ መስኖ ውሃ ቀስ በቀስ እየጐደለ ይደርቃል፤ ደንገሎቹና ቀጤማዎቹ ይጠወልጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መስኖዎቹ ይከረፋሉ፤ የግብጽ ጅረቶች ይጐድላሉ፤ ይጠፋሉም። ደንገሉና ቄጠማውም ይጠወልጋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መስኖዎቹም ይከረፋሉ፥ የግብጽም ጅረቶች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገሉና ቄጠማውም ይጠወልጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዞችም ይነጥፋሉ። ቦዮችና መስኖች ያንሳሉ፤ ይደርቃሉም፤ ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፥ ደንገልና ቄጠማ ይጠወልጋሉ። |
ሆኖም ከዚያ በላይ ልትሸሽገው አለመቻልዋን በተረዳች ጊዜ፥ በሣጥን መልክ ከደንገል የተሠራ ቅርጫት አዘጋጀች፤ ውሃም እንዳያስገባ በቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም አስገብታ ቅርጫቱን በወንዝ ዳር በሚገኝ ቀጤማ መካከል አስቀመጠችው።
ያቺ አገር መልእክተኞችን ከደንገል በተሠራ ጀልባ በአባይ ወንዝ ላይ ትልካለች፤ ሕዝብዋ ረጃጅሞችና ቆዳቸው ለስላሳ፥ አገራቸው በወንዞች የተከፋፈለች፥ ጠንካሮችና ኀያላን በመሆናቸው በዓለም ሁሉ ወደሚፈሩት ሕዝቦች እናንት ፈጣን መልእክተኞች ሂዱ!
ነነዌ ሆይ! አንቺም የውሃ መከላከያ እንዳለሽ ሁሉ በአባይ ወንዝ አጠገብ ከነበረችው፥ ዙሪያዋ በውሃ ከተከበበው፥ የባሕር ውሃም መከላከያዋ ከሆነው ከግብጽ ከተማ ከቴብስ ትበልጫለሽን?