ኢሳይያስ 19:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግብጽ ባለጸጋም ሆነ ድኻ፥ ዝነኛ የሆነ ወይም ታዋቂነት የሌለው ምንም ነገር ማድረግ አይችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራስም ይሁን ጅራት፣ የዘንባባ ዝንጣፊም ይሁን ደንገል፣ ለግብጽ የሚያደርጉላት አንዳች ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራስ ይሁን ጅራት፥ የዘንባባ ዝንጣፊ ይሁን ደንገል፥ ለግብጽ አንዳች ነገር ሊያደርጉላት አይችሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለግብፃውያን ራስ ወይም ጅራት፥ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ያለው ሥራ የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራስ ወይም ጅራት የሰሌን ቅርንጫፍ እንግጫ ቢሆን ሊሰራ የሚችል ሥራ ለግብጽ አይሆንላትም። |
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥
እነሆ በዚህ ምክንያት በተራሮች ላይ በእህል፥ በወይን፥ በዘይት፥ ምድር በምታበቅለው ሁሉ ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶች፥ በሥራቸውም ውጤት ሁሉ ላይ ድርቅን አመጣለሁ።”