የሞአብ ሕዝቦች የጣዖት ቤተ መቅደሶቻቸውና መስገጃዎቻቸው ወደተሠሩበት ተራራ ለጸሎት በመመላለስ ሰውነታቸውን አድክመዋል፤ ነገር ግን ይህ ሁሉ ምንም ውጤት አያስገኝላቸውም።
ኢሳይያስ 16:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ስለ ሞአብ በቅድሚያ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ሞዓብ የተናገረው ቃል ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በሞዓብ ላይ አስቀድሞ የተናገረው ነገር ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በሞዓብ ላይ በድሮ ዘመን የተናገረው ነገር ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በሞዓብ ላይ በድሮ ዘመን የተናገረው ነገር ይህ ነው። |
የሞአብ ሕዝቦች የጣዖት ቤተ መቅደሶቻቸውና መስገጃዎቻቸው ወደተሠሩበት ተራራ ለጸሎት በመመላለስ ሰውነታቸውን አድክመዋል፤ ነገር ግን ይህ ሁሉ ምንም ውጤት አያስገኝላቸውም።
አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአንድ ጊዜያዊ የቅጥር ሠራተኛ የሥራ ጊዜ እንደሚቋረጥ የሞአብ ክብርና ብዙ ሕዝቦችዋ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይዋረዳል፤ ከሕዝቧ የተረፉትም በጣም ጥቂቶችና ደካሞች ይሆናሉ።”
እናንተ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ አስቀድሜ አልነገርኳችሁምን? ወይስ አልገለጽኩላችሁምን? ለዚህም እናንተ ምስክሮቼ ናቸሁ፤ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ከእኔ ሌላ መጠጊያ አለት የለም፤ ማንም የለም።”