ኢሳይያስ 14:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ የልጆቹ መታረድ አሁኑኑ ይዘጋጅ፤ የዚህ ንጉሥ ልጆች በቀድሞ አባቶቻቸው ኃጢአት የሞት ፍርድ ይጠብቃቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ከእነርሱ ማንም ምድርን መውረስም ሆነ ከተሞችን መሥራት አይችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተነሥተው ምድርን እንዳይወርሱ፣ ዓለምንም በከተሞቻቸው እንዳይሞሉ፣ ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት፣ ወንድ ልጆቹ የሚታረዱበትን ስፍራ አዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳይነሱም፥ ምድርንም እንዳይወርሱ፥ የዓለሙንም ፊት በከተሞች እንዳይሞሉ ስለ አባቶቻቸው በደል ለልጆቹ ሞትን አዘጋጁላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዳይነሡም፥ ምድርንም እንዳይወርሱ፥ የዓለሙንም ፊት በጦርነት እንዳይሞሉ በአባቶቻቸው በደል ይገድሉአቸው ዘንድ ልጆችህን አዘጋጅ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳይነሱም፥ ምድርንም እንዳይወርሱ፥ የዓለሙንም ፊት በከተሞች እንዳይሞሉ ስለ አባቶቻቸው በደል ለልጆቹ ሞትን አዘጋጁላቸው። |
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም በምድር ላይ ስለ ፈሰሰው የጻድቃን ደም ቅጣቱ በእናንተ ላይ ይደርሳል፤