ኢሳይያስ 10:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጠላት ሠራዊት ወደ ዓይ ከተማ ደረሰ፤ በሚግሮንም በኩል ሲያልፉ ጓዛቸውን በሚክማስ አኖሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ዐያት ይገባሉ፣ በሚግሮን ያልፋሉ፤ ጓዛቸውንም በማክማስ ያከማቻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዐያት ይገባሉ፤ በሚግሮን ያልፋሉ፤ ጓዛቸውንም በማክማስ ያከማቻሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አንጋይ ከተማ ይመጣል፤ በመጌዶን በኩል ያልፋል፤ በማክማስም ውስጥ ዕቃውን ያኖራል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አንጋይ መጥቶአል፥ በመጌዶን በኩል አልፎአል፥ በማክማስም ውስጥ ዕቃውን አኑሮአል፥ |
በኀይል እየጐረፈም ወደ ይሁዳ ምድር ይገባል፤ ሁሉን ነገር አጥለቅልቆ ከመሸፈን አልፎ ሙላቱ እስከ አንገት ይደርሳል፤” ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ እርሱም ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሰውራ እንደምትጠብቅ ምድሪቱን ይጠብቃል።
የሰማርያ ቊስል ሊፈወስ የሚችል አይደለም፤ ይህም ሥቃይ ወደ ይሁዳ ደርሶአል፤ ሕዝቤ ወደሚሰበሰቡበት ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይም ተዛምቶአል።”
ኢያሱ በኢያሪኮ ሳለ በቤትአዌን አጠገብ ከቤትኤል በስተምሥራቅ የምትገኘውን “ዐይ” ተብላ የምትጠራውን ከተማና የምድሪቱን አቀማመጥ አጥንተው ይመለሱ ዘንድ ጥቂት ሰዎችን ላከ። ይህንንም በትእዛዙ መሠረት ከፈጸሙ በኋላ፥
ከእስራኤል ሕዝብ መካከል የተውጣጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን መረጠ፤ ከእነርሱ መካከል ሁለቱን ሺህ በሚክማስና በቤትኤል በሚገኘው ኮረብታማ አገር ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ መደበ፤ አንዱን ሺህ ሰዎች ደግሞ ከልጁ ከዮናታን ጋር በማሰለፍ በብንያም ነገድ ግዛት ውስጥ ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ኮረብታማ አገር ላከ፤ ከዚህ የተረፉትን ሌሎች ሰዎች ግን ወደየቤታቸው አሰናበተ።
ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ።
በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከሚክማስ እስከ አያሎን ባለው መንገድ ሁሉ እያሳደዱ በመውጋት ፍልስጥኤማውያንን ድል መቱ፤ በዚህም ጊዜ እስራኤላውያንም በራብ እጅግ ዝለው ነበር።
ከአለቶቹም አንዱ ከመተላለፊያው በስተ ሰሜን በኩል በሚክማስ ፊት ለፊት የሚገኘው ሲሆን፥ ሁለተኛውም በስተደቡብ በኩል በጌባዕ ፊት ለፊት ይገኝ ነበር።