ዕብራውያን 9:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በድንኳኒቱና በመገልገያ ዕቃ ሁሉ ላይ ደምን ረጨ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ድንኳኒቱንና ማገልገያ ዕቃውን ሁሉ በደም ረጨው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተመሳሳይ በድንኳኒቱና በማገልገያው ዕቃ ሁሉ ደምን ረጭቷል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንኳኑንና የመገልገያውን ዕቃ ሁሉ በደሙ ይረጭ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም በድንኳኒቱና በማገልገያው ዕቃ ሁሉ ደምን ረጨ። |
እርሱንም ዕረድና ከደሙ ጥቂት ወስደህ የአሮንንና የልጆቹን ቀኝ ጆሮዎች ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ትቀባለህ፤ የተረፈውንም ደም በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ርጨው።
ስለ ኃጢአትም ይቅርታ በእያንዳንዱ ቀን አንድ ኰርማ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤ ይህም መሠዊያውን ያነጻል፤ የተቀደሰም ይሆን ዘንድ የወይራ ዘይት ቀባው።
ሙሴም ዐረደው፤ ከደሙም ጥቂት በጣቱ ነክሮ የመሠዊያውን አራት ማእዘን ጒጦች በመቀባት አንጽቶ ቀደሰው፤ ከዚያም የተረፈውን ደም በመሠዊያው ሥር አፈሰሰው፤ በዚህም ዐይነት መሠዊያውን ለእግዚአብሔር በመለየት አነጻው፤
በሬውንና የበግ አውራውን ዐርዶ ስለ ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት በማድረግ አቀረበ፤ ልጆቹም ደሙን አመጡለት፤ እርሱም ተቀብሎ ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨው፤