“በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚከናወነው ተግባር መገልገያ ይሆኑ ዘንድ እነዚህን መባዎች ተቀበል፤ ለእያንዳንዳቸው አገልግሎት በሚያስፈልጋቸው መጠን መድበህ ለሌዋውያን ስጣቸው።”
ዕብራውያን 13:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ መሠዊያ አለን፤ ሆኖም በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት በዚህ መሠዊያ ላይ ካለው ምግብ ወስደው መብላት አይፈቀድላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንኳኒቱም የሚያገለግሉ ከዚያ ሊበሉ መብት ያላገኙበት መሠዊያ አለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሠዊያ አለን፤ ሆኖም ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ ከእርሱ የመብላት መብት የላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንኳኒቱን ሲያገለግሉ የነበሩ ካህናት ከእርሱ ሊበሉ የማይቻላቸው መሠዊያ አለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሠዊያ አለን፥ ከእርሱም ሊበሉ ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ መብት የላቸውም። |
“በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚከናወነው ተግባር መገልገያ ይሆኑ ዘንድ እነዚህን መባዎች ተቀበል፤ ለእያንዳንዳቸው አገልግሎት በሚያስፈልጋቸው መጠን መድበህ ለሌዋውያን ስጣቸው።”
አይደለም! አሕዛብ መሥዋዕት የሚያቀርቡት ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአጋንንት ነው፤ ስለዚህ እናንተ ከአጋንንት ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አልፈልግም፤
በቤተ መቅደስ የሚያገለግሉ ምግባቸውን ከቤተ መቅደስ እንደሚያገኙና በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት የሚያቀርቡና የሚያገለግሉ ከመሥዋዕት ተካፍለው እንደሚበሉ ታውቁ የለምን?
እነዚህ ካህናት የሚያገለግሉበት ድንኳን በሰማይ ለሚገኘው ምሳሌና ጥላ ብቻ ነው፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኒቱን በሚሠራበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር “በተራራው ላይ እንደ ተገለጠልህ ዐይነት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ አድርግ” ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው።