ዕብራውያን 11:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አመንዝራይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙት ጋር ከመሞት የተረፈችው በእምነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዝሙት ዐዳሪዋ ረዓብ፣ ሰላዮቹን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙት ጋራ ያልጠፋችው በእምነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው በእምነቷ ምክንያት ከማይታዘዙ ጋር አልጠፋችም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘማ ረአብም በእምነት ከከሓዲዎች ጋር አልጠፋችም፤ ጕበኞችን በሰላም ተቀብላ ሰውራቸዋለችና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙ ጋር በእምነት አልጠፋችም። |
አመንዝራይቱ ረዓብ የእስራኤልን መልእክተኞች በቤትዋ በተቀበለች ጊዜና በሌላም መንገድ እንዲሄዱ ባደረገቻቸው ጊዜ እርስዋስ በሥራዋ ጸድቃ የለምን?
ደግሞም፥ “እነሆ! ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ፤ እነሆ! ሰዎችን አደናቅፎ የሚጥል አለት” ይላል። እነርሱ ቃሉን ባለማመናቸው ይሰናከላሉ፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።
እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።