ዘፍጥረት 44:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍም “ይህ ያደረጋችኹት ነገር ምንድን ነው? እኔ ባለሁበት ደረጃ የሚገኝ ሰው በተለየ ጥበብ ሁሉን ነገር መርምሮ ማወቅ የማይችል መሰላችሁን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም፣ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን?” ሲል ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም፥ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን?” ሲል ጠየቃቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም፥ “ይህ ያደረጋችሁት ነገር ምንድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥጢርን እንዲያውቅ አታውቁምን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ይህ ያደረጋችሁት ነገር ምንድር ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥጢርን እንድያውቅ አታውቁምን? አላቸው። |
እርሱ ግን ይህን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ ስለዚህም እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሁሉንም ነገር በእኔ ኀላፊነት ሥር ስላደረገ፥ በቤቱ ውስጥ ስላለው ንብረት ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ ያለውን ንብረት ሁሉ እንዳስተዳድርለት በዐደራ ለእኔ ሰጥቶኛል።
ይሁዳም “እንግዲህ ለጌታችን ምን መልስ እንሰጣለን? ራሳችንን ነጻ የምናደርግበት መልስ መስጠት ከቶ አንችልም፤ እግዚአብሔር የሠራነውን በደል ገልጦታል፤ እንግዲህ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሪያዎችህ እንሁን” አለ።
ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እዚያ ብዙ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ በአንድነት በመሰብሰብ አሮንን ከበው “ያ ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ በፊት በፊታችን እየሄዱ የሚመሩን አማልክትን ሥራልን” አሉት።